Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

መልዕክት ለወጣቶች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ተነፃፃሪ ትምህርት

    በእስራኤላውያን ዘመን እንደነበር ሁሉ ዛሬም እያንዳንዱ ወጣት የተግባራዊ ሕይወት ስራዎችን መማር አለበት፡፡ አስገዳጅ ሁኔታዎች ሲከሰቱ ለሕይወት የሚያስፈልጉ ነገሮችን ሰርቶ ማግኘት እንዲችል የሆነ የእጅ ሥራ ዘርፍ እውቀት ማግኘት አለበት፡፡ ይህ አስፈላጊ የሚሆነው ለሕይወት አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን ለማሟላት ብቻም ሳይሆን ለአካል፣ ለአእምሮና ለግብረገብ እድገት ካለው ጠቀሜታ አንፃርም ነው፡፡ ምንም እንኳን አንድ ግለሰብ ራሱን ለመርዳት የግድ የእጅ ሥራ መስራት ባይኖርበትም ሥራን ግን መማር አለበት፡፡ ያለ አካል እንቅስቃሴ ማንም ሰው የተስተካከለ የሰውነት አቋምና ጤንነት ሊኖረው አይችልም፡፡ ተገቢ ቁጥጥር የሚደረግበትን የጉልበት ሥራ መማር ጠንካራና ንቁ የሆነ አእምሮና የከበረ ባሕርይ እንዲኖረን የማድረግ ጠቀሜታውም ለአካል ጤንነትና ለተስተካከለ አቋም ከሚሰጠው ጠቀሜታ ያነሰ አይደለም፡፡MYPAmh 117.2

    የተግባር ሥራ እውቀት ሳይታከልበት የመጽሐፍ እውቀት ብቻ ያገኙ ተማሪዎች የተሟላ ትምህርት አግኝተናል ማለት አይችሉም፡፡ ለተለያየ የሥራ ዘርፍ መዋል የሚችል ኃይል ችላ ተብሏል፡፡ ትምህርት የሚያካትተው አእምሮን ብቻ መጠቀምን አይደለም፡፡ የጉልበት ሥራ ለእያንዳንዱ ወጣት ሊሰጥ ከሚገባው ስልጠና አንዱ ክፍል ነው፡፡ አንድ ተማሪ ጠቃሚ የሆነ የጉልበት ሥራ ትምህርት ካላገኘ የትምህርት ጠቃሚ የሆነው ክፍል ቀርቷል ማለት ነው፡፡MYPAmh 117.3

    ጤናማ የሆነ አጠቃላይ የአካል እንቅስቃሴ ሰፊና ሁሉን ያካተተ ትምህርትን ይሰጣል፡፡ እያንዳንዱ ተማሪ ከቀን ውስጥ የተወሰነውን ሰዓት ለጉልበት ሥራ ማዋል አለበት፡፡ ያኔ የሥራ ልምድ ይፈጠርና በራስ የመተማመን መንፈስ ይደፋፈራል፡፡ እግረ መንገዱንም ወጣቶች ሥራ ከመፍታት የተነሳ ከሚከሰቱ ክፉና አዋራጅ ተግባራት ይጠበቃሉ፡፡ ይህ ሁሉ የሚሆነው ከትምህት የመጀመሪያ አላማ ጋር አብሮ መጓዝ ሲቻል ነው፡፡ ሥራን፣ ትጋትንና ንጽህናን ስናደፋፍር ከፈጣሪ ጋር እየተስማማን ነን፡፡MYPAmh 117.4

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents