Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

መልዕክት ለወጣቶች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    መዝገብ በሰማይ

    የእግዚአብሔር ሥራ ወደ ልባችን ተጠግቶ መቀመጥ አለበት። ለአንድ ቤተሰብ በረከት የሆነ የእውነት ብርሃን በወላጆችና በልጆች አማካኝነት ለሌሎች ቢተላለፍ ኖሮ ለሌሎች ቤተሰቦችም ታላቅ በረከት ይሆን ነበር:: ነገር ግን በልግስናና በብዛት የተሰጡ የእግዚአብሔር ሀብቶች ለእርሱ በሚከለከሉበት ጊዜ እና በራስ ወዳድነት ለራሳችን በሚሆኑበት ጊዜ በበረከቶቹ ፋንታ የእግዚአብሔርን እርግማን እንቀበላለን! ይህንን ጌታ ተናግሮታልና የእግዚአብሄር የይገባኛል ጥያቄ ከማንኛውም ጥያቄ ቅድሚያ ተሰጥቶት በመጀመሪያ መፈፀም አለበት። ቀጥሎ ድሆችና ችግረኞች ሊረዱ ይገባል። ይህ ለእኛ የፈለገውን ያህል ዋጋ ቢያስከፍለንም ወይም መስዋዕትነት ቢጠይቅብንም ችላ ሊባል አይገባም።MYPAmh 198.3

    “በቤቴ መብል ይሆን ዘንድ…::” በአመጋገባችን፣ በምንጠጣውና በአለባበሳችን፣ በነገር ሁሉ እራሳችንን መግዛት ሃላፊነታችን ነው። ለእግዚአብሔር የእርሱን ድርሻ በአሥራት መልክ ብቻ መመለስ ሳይሆን በተቻለ መጠን በስጦታ መልክም ለመመለስ ፍላጎት ባለው ልብ ውስጥ የህንፃ ግንባታና የቤት ቁሳቁሶች ግዥም በጥንቃቄ መታየት አለባቸው ። እግዚአብሔር የራሱ እንደሆነ የሚናገረውንና ስጦታዎችን በጌታ ጎተራ ውስጥ በማከማቸት ለራሳቸው በሰማይ መዝገብ እያጠራቀሙ ያሉ እጅግ ብዙዎች ሊኖሩ ይችላሉ።MYPAmh 198.4

    የራሳቸው ንብረት እንደሆነ ከሚቆጥሩት ንብረት ውስጥ እግዚአብሔር ከእነርሱ ምን እንደሚፈልግ ለማወቅ በታማኝነት እየጠበቁ ያሉ ሰዎች የብሉይ ኪዳን ጥቅሶችን መመርመር አለባችው። በዚህ ረገድ በረጅሙ የምድረ በዳ ጉዞ የእስራኤል የማይታይ መሪ የነበረው ክርስቶስ ህዝቡ እንዲፈጽሙ የሰጣቸውን መመሪያ ማየት ያስፈልጋቸዋል። ወደ ጎተራው መምጣት የሚገባውን ከእግዚአብሔር ከምንዘርፍ ይልቅ በግላችን በማንኛውም የማይመች ሁኔታ ውስጥ ለመግባት፣ በማንኛውም ችግር ውስጥ ለማለፍ ፍቃደኛ መሆን አለብን። የመጽሐፍ ቅዱስ አንባቢዎችና በመጽሐፍ ቅዱስ የሚያምኑ ሁሉ በዚህ ጉዳይ ላይ ጌታ ምን እንደሚል ምሁራዊ እውቀት ይኖራቸዋል።MYPAmh 198.5

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents