Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

መልዕክት ለወጣቶች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ከሁሉ የሚበልጥ ትምህርት

    አንባቢው አባውንና ነቢያትን ማነጋገር ይችላል፣ እጅግ አነሳሽ በሆኑ ሁኔታዎች ውስጥ መጓዝ ይችላል፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር እኩል የነበረውና በሰማይ ንጉሥ የነበረው ክርስቶስ ወደ ሰብዓዊነት ደረጃ ዝቅ ሲልና የደህንነትን እቅድ ሲሰራ፣ ሰይጣን ሰውን አስሮበት የነበረውን ሰንሰለት ሲሰብርና እግዚአብሔርን የሚመስል ሰውነት መልሶ ማግኘትን የሚቻል ሲያደርግለት ማየት ይችላል፡፡ የክርስቶስ ሰብዓዊነትን መልበስ፣ ለሰላሣ ዓመት በሰው ደረጃ መቆየት፣ ከዚያም በኋላ ሰው እንዲጠፋ ላለመተው ነፍሱን የኃጢአት መስዋዕት አድርጎ መስጠት በጥልቅ ማሰብንና እጅግ የተቀደሰ ጥናት የሚሻ ትምህርት ነው…፡፡MYPAmh 167.1

    አእምሮ የአስደናቂ እውነቶችን ራዕይ ከጨበጠ ኃይሎቹን በማይረቡ ጉዳዮች ላይ በማዋል በፍጹም አይረካም፡፡ የዛሬ ወጣቶችን እያዋረዱ ያሉ ቆሻሻ ሥነ-ጽሁፎቸንና ሥራ የሚያስፈቱ መደሰቻዎችን በመጸየፍ ይሸሹአቸዋል፡፡ ከመጽሐፍ ቅዱስ ገጣሚዎችና ልቃውንት ጋር የተገናኙና ነፍሶቻቸው በእምነት ጀግኖች ግርማ በተሞሉ ሥራዎች የተቀሰቀሱ ሰዎች እጅግ አንቱ ከተባሉ ሥጋዊ ደራሲያን ቢማሩ ኖሮ ወይም የዓለምን ፈርዖኖች፣ ሄሮድሶችና ቄሳሮችን ብዝበዛ በማሰላሰልና በማግነን ከሚያገኙት እውቀት በበለጠ ሁኔታ ልባቸው እጅግ ንፁህ ይሆንና አእምሮአቸው በጣም ከፍ ብሎ ይወጣሉ፡፡ የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት እንደሆነ ስለማይቀበሉ የወጣቶች ኃይላት በአብዛኛው ኃይል የለሽ ናቸው፡፡ እግዚአብሔር ለዳንኤል ጥበብና እውቀት የሰጠው ከእምነቱ መርሆዎች ውስጥ ጣልቃ ከሚገባ ከማንኛውም ኃይል ተጽእኖ ሥር እንዳይሆን ነበር፡፡ MYPAmh 167.2

    አእምሮ ያላቸው፣ የተረጋጉና ከፍ ያለ ዋጋ ያላቸው ጥቂት ሰዎች ያሉን ምክንያቱ አብዛኞቹ ራሳቸውን ከሰማይ በመለየት ታላቅነትን ለማግኘት ስለሚያስቡ ነው፡፡MYPAmh 167.3

    እግዚአብሔር በሰው ልጆች አልተፈራም፣ አልተወደደም፣ አልተከበረም፡፡ ኃይማኖት የሚነገረውን ያህል አልተኖረበትም፡፡ እግዚአብሔር ለሰው ልጅ ብዙ ነገር ማድረግ ያልቻለበት ምክንያት ሰው በቀላሉ ራሱን ከፍ ከፍ የሚያደርግና በቀላሉ ውጤቱን ያመጠው ራሱ እንደሆነ የሚያስብ በመሆኑ ነው፡፡ እግዚአብሔር እኛን የፈጠረው ችሎታዎቻችንን እንድናሰፋና ሊገኝ የሚችለውን አጋጣሚ ሁሉ ለመጠቀም ራሳችንን እንድናዘጋጅ፣ ማስተዋላችንን እንድናሳድግና እንድንጠነክር ነበር፡፡ ሰው አሁን እያጎለበተ ካለው የበለጠ ከፍ ላለና የከበረ ሕይወት ነበር የተወለደው፡፡ በዚህ ሟች በሆነ ሕይወት የምንኖረው ጊዜ በእግዚአብሔር ሕይወት ለሚለካ ኑሮ ዝግጅት ነው፡፡MYPAmh 167.4

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents