Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

መልዕክት ለወጣቶች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የተሳሳተ የሙዚቃ አጠቃቀም

    መላእክት በመኖሪያ አካባቢያችሁ •እየተንሳፈፉ ናቸው። ወጣቶች እዚያ ስለተሰበሰቡ በድምፅና በመሳሪያ የታጀበ የሙዚቃ ድምጽ አለ! ክርስቲያኖች በዚያ ተሰብስበዋል፣ ነገር ግን ያ የምትሰሙት ምንድን ነው? •እየተሰማ ያለው ለዳንስ ቤት ገጣሚ የሆነ የማይረባ መዝሙር ነው። እነሆ ንፁሃን መላእክት ብርሃናቸውን በዙሪያቸው ይሰበስባሉ፣ በዚያ ቤት ውስጥ ያሉትንም ጨለማ ይሸፍናቸዋል። መላእክት ከቦታው እየሄዱ ናቸው። በፊታቸው ሀዘን ይታያል። እነሆ እያለቀሱ ናቸው። ይህንን በሁሉም ደረጃ ባሉ ሰንበት ጠባቂዎች ዘንድ በተለይም በ______ ባሉት ብዙ ጊዜ ተደጋግሞ አየሁ። ለፀሎት መሰጠት የሚገባቸውን ሰዓቶች ሙዚቃ ይዞባቸዋል። ሙዚቃ ብዙ ሰንበት ጠባቂዎች ነን የሚሉ ክርስቲያኖች እያመለኩት ያለ ጣኦት ነው። ሰይጣን ወደ ወጣቶች አእምሮ ለመድረስ የሚያገለግል መንገድ እስከሆነለት ድረስ ሙዚቃን አይቃወምም። አእምሮን ከእግዚአብሔር የሚለይና ለእርሱ ክብር ሊውል የሚችለውን ሰዓት የሚይዝ ማንኛውም ነገር ለሰይጣን አላማ ገጣሚ ይሆናል። አብዛኛውን ቁጥር ለመያዝና እጅግ ከባድ ተፅዕኖ ሊያሳድር በሚችልበት መንገድ በሞኝ (ስድ) ፍቅር አማካኝነት በኃይሉ ሽባ ሆነው እያሉ ይሰራል። ለመልካም ተግባር ከዋለ ሙዚቃ በረከት ነው። ነገር ግን ብዙ ጊዜ ነፍሳትን ለማጥመድ ሰይጣን ከሚጠቀምባቸው እጅግ ማራኪ ከሆኑ መንገዶች አንዱ ሆኗል:: ያለ አግባብ ጥቅም ላይ ሲውል ያልተቀደሱትን ሰዎች ወደ ኩራት፣ ከንቱነትና ሞኝነት ይመራል። የፀሎትና የአምልኮ ቦታን እንዲወስድ ሲፈቀድለት አሰቃቂ እርግማን ነው። ለዝማሬ የሚሰበሰቡ ወጣቶች፣ ክርስቲያኖች ቢሆኑም ብዙ ጊዜ በከንቱ ንግግራቸውና በሚመርጡት የሙዚቃ አይነት አምላካቸውንና እምነታቸውን ያዋርዳሉ። የተቀደሰ ሙዚቃ ለእነርሱ ፍላጎት የሚገጥም አይደለም። ብዙዎች ሳያስተውሉት ወዳለፉት ግልፅ ወደ ሆነው የእግዚአብሔር ቃል ትምህርት ተመራሁ። በፍርድ ቀን እነዚህ የተገለጡ ቃላት በሙሉ ለመስማት ፈቃደኛ ያልሆኑትን ይኮንኗቸዋል። Testimonies for the church, Vol. 1, P 506MYPAmh 192.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents