Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

መልዕክት ለወጣቶች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ለክርስቶስ መገዛት

    በልዑል አማኑኤል ደም በተቀለመው ባንዲራ ሥራ የቆሙ በክርስቶስ ሠራዊት ውስጥ ታማኝ ወታደሮች መሆን አለባቸው። በፍፁም አመፀኞችና ውሸታሞች መሆን የለባቸውም:: ብዙ ወጣቶች የሕይወት መስፍን ለሆነው ለኢየሱስ ለመቆም ፈቃደኛ ይሆናሉ። ነገር ግን ከእርሱ ጋር ቆመው መቀጠል ከፈለጉ አዛዣቸው ወደ ሆነው ኢየሱስና ወደ መመሪያዎቹ ሁል ጊዜ መመልከት አለባቸው። ከሰይጣን ጋር ህብረት ፈጥረውና እርሱን እየረዱ እያሉ የክርስቶስ ወታደሮች መሆን አይችሉም። ምክንያቱም ከሰይጣን ጋር እስከተባበሩ ድረስ የክርስቶስ ጠላቶች ስለሚሆኑ ነው። ቅዱስ አመኔታዎችን አሳልፈው ይሰጣሉ፡፡ ከሰይጣንና ታማኝ ወታደሮቹ ጋር ግንኙነት ይፈጥሩና በነዚህ ሕያው ወኪሎቹ አማካይነት ጠላት የክርስቶስ ወታደሮችን ልብ ለመስረቅ ያለማቋረጥ ይሰራል።MYPAmh 92.5

    የክርስቶስ ወታደሮች እንደሆናችሁ የምትናገሩትን ውድ ወጣቶችን የትኞቹን ጦርነቶች እንደተዋጋችሁ እንድትነግሩኝ እጠይቃችኋለሁ:: ምድብ ሥራችሁ ምን ነበር? የእግዚአብሐየር ቃል በግልፅ ሥራችሁን ሲገልፅላችሁ ከዝንባሌያችሁ ጋር ስላልተጣጣመ እምቢ ብላችኋልን? የዓለም ብልጭልጭ ለኢየሱስ መስጠት ያለባቸሁን አገልግሎት እንዳትሰጡ አታልሎአችኋልን? ሰይጣን ውስብስብ ማታለያዎችን በማዘጋጀት ሥራ ላይ ተሰማርቷል። ትንንሽ በሚመስሉ ነገሮች ላይ የእግዚአብሔርን ፈቃድMYPAmh 93.1

    እንድትጥሱ በማድረግ ከኢየሱስ ወደ ራሱ ይመልሳችኋል። ስምህ በቤተክርስቲያን መዝገብ ላይ ሊኖርና የእግዚአብኼር ልጅ ነኝ ልትል ትችላለህ። ነገር ግን የምታሳየው ምሳሌነትህና በሌሎች ላይ የምታሳድረው ተጽእኖህ ለክርስቶስ ባሕሪይ የተሳሳተ መግለጫ ይሰጥና ሌሎችን ከኢየሱስ ያርቃቸዋል። ነፍሱ ሙሉ በሙሉ እግዚአብሔር እንዲሰራ ለሰጠው ሥራ ያልዋለ አማኝ ደስታ፣ ሰላም ወይም ፍስሐ የለውም። እንደዚህ ዓይነቱ ግለሰብ በንስሀና በኑዛዜ ራሱን ለእግዚአብሔር አሳልፎ በመስጠት ሳይሆን ራሱን የበለጠ ለዓለም በማስገዛትና በጦርነቱ ላይ በክርስቶስ ወገን ሳይሆን በሰይጣን ወገን በመሰለፍ ያለማቋረጥ ዓለምን ወደ ቤተክርስቲያን እያመጣ ነው።MYPAmh 93.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents