Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

መልዕክት ለወጣቶች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የታዛዥነት መዳረሻ

    ወጣቶች ዘላለማዊ መዳረሻቸውን አሁን እየወሰኑ ናቸው። ስለዚህ “እግዚአብሔር አምላክህ በሚሰጥህ ምድር እድሜህ ይረዘም ዘንድ” የሚለውን ቃል ኪዳን እግዚአብሔር የሰጠበትን ትዕዛዝ እንድታስቡት እማፀናኋለሁ። ልጆች፣ ዘላለማዊ ሕይወት ትመኛላችሁን? ከሆነ ወላጆቻችሁን አክብሩ…።MYPAmh 215.4

    እነርሱን ባለመውደድና ባለመታዘዝ ኃጢአት ሠርታችሁ ከሆነ ያለፈውን ጊዜ መዋጀትን አሁን ጀምሩ:: ሌላ መንገድን መምረጥ ዘላለማዊ ሕይወትን ማጣት ስለሆነ ውጤቱን መሸከም አትችሉም። ልብን የሚመረምር አምላክ ለወላጆቻችሁ ያላችሁን አመለካከት ያውቃል። እርሱ የግብረገብ ባሕርያችንን በሰማያዊ ቤተ-መቅደስ ውስጥ ባለው ወርቃማ ሚዛን እየመዘነ ነው። እነሆ ወላጆቻችሁን ችላ ማለታችሁን፣ ለእነርሱ ያሳያችሁትን ግድየለሽነታችሁንና የተቀደሰውን የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ መናቃችሁን ተናዘዙ።MYPAmh 215.5

    የወላጆቻችሁ ልቦች ለእናንተ የለሰለሱና ርህራሄ ያላቸው ሆነው ሳለ እናንተ ፍቅራቸውን አመስጋኝነት በሌለው ቅዝቃዜ ትመልሳላችሁን? እነርሱ ነፍሶቻችሁን ይወዳሉ፣ እንድትጸኑም ይፈልጋሉ፡፡ ነገር ግን ብዙ ጊዜ ምክራቸውን በመናቅ የራሳችሁን ፈቃድ አልፈጸማችሁምን? የራሳችሁን መንገድ አልተከተላችሁምን? እንደዚህ ዓይነት የትዕቢት እርምጃ በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን እያወቃችሁ የራሳችሁን ውሳኔ አልተከተላችሁምን? ብዙ አባቶችና እናቶች ከልጆቻቸው አመስጋኝ ካለመሆንና አክብሮት ከማጣት የተነሣ በተሰበረ ልብ ወደ መቃብሮቻቸው ወርደዋል፡፡ The youth’s Instructor, June 22, 1893.MYPAmh 215.6

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents