Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

መልዕክት ለወጣቶች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ለእያንዳንዱ ነፍስ የሚደረግ ጦርነት

    ክፉ መላእክት ነፍሳትን ለማጥፋት ሲታገሉና የእግዚአብሔር መላእክት ሲቃወሙአቸው አየሁ፡፡ ጦርነቱ ከባድ ነበር፡፡ ክፉ መላእክት በነፍሳት ዙሪያ ሲተረማመሱና ከባቢ አየሩን በመርዘኛ ተጽእኖአቸው ሲበክሉትና የማገናዘብ ችሎታቸውን ሲያደድቡት ነበር፡፡ ቅዱስ መላእክት እነዚህን ነፍሳት በንቃት እየጠበቋቸው የሰይጣንን ሰራዊት ለማባረር ይጠብቁ ነበር፡፡ ነገር ግን የጥሩ መላእክት ሥራ ከግለሰቦቹ ፈቃድ ውጭ አእምሮአቸውን መቆጣጠር አልነበረም፡፡ እነርሱ ለሰይጣን ከተሸነፉና ለመቋቋም ምንም ጥረት የማያደርጉ ከሆነ የእግዚአብሔር መላእክት እነዚህ አደጋ ውስጥ ያሉ ነፍሳት ለእርዳታ ነቅተው ወደሰማይ እንዲመለከቱ እስኪያነሳሱአቸው ድረስ የሰይጣን ሰራዊት እንዳያጠፉአቸው ከመቆጣጠር ያለፈ ሊያደርጉት የሚችሉት ነገር አይኖርም፡፡ ራሳቸውን ለመርዳት ምንም ጥረት የማያደርጉትን ነፃ ለማውጣት ኢየሱስ መላእክቱን አይልክም፡፡MYPAmh 40.6

    ሰይጣን አንድን ነፍስ የማጣት አደጋ መኖሩን ካየ ያንን አንድ ነፍስ በቁጥጥሩ ሥር ለማቆየት ራሱን እስከመጨረሻ ያስጨንቃል፡፡ ግለሰቡ አደጋውን ከተገነዘበና በሐዘንና በጠለቀ ስሜት ብርታት ለማግኘት ወደ ኢየሱስ ከተመለከተ ሰይጣን ምርኮኛውን እንዳያጣው በመፍራት ተጨማሪ የእርሱ መላእክት ያቺን ምስኪን ነፍስ እንዲከቧትና የሰማይ ብርሃን እንዳይደርሳት በዙሪያዋ የጨለማ ግድግዳ እንዲሰሩ ይጠራል፡፡ ነገር ግን ያቺን ነፍስ ተስፋ ባለመቁረጥ ረዳተ-ቢስነትዋንና ደካማነትዋን በማስተዋል ራስዋን በኢየሱስ ደም በተደረገላት ሥራ ላይ ስትጥል ኢየሱስ ያንን ልባዊ የሆነ የእምነት ፀሎት በመስማት በኃይል ከክፉ መላእክት የሚበልጡትን የራሱን ተጨማሪ የመላእክት ሰራዊት በመላክ ነፃ ያወጣታል፡፡MYPAmh 41.1

    ሰይጣን ብርቱ በላንጣው በሆነው በክርስቶስ ብርታትና ግርማ ፊት ለመቆም ስለሚፈራና ስለሚንቀጠቀጥ የነፍሳት ጥያቄ በየሱስ ፊት ሲቀርብ መታገስ አይችልም፡፡ ልባዊ የሆነ የፀሎት ድምፅ ሲሰሙ የሰይጣን ሰራዊት በሙሉ ይብረከረካሉ፡፡ በኃይል የተሞሉ መላእክት የሰማይን የጦር ዕቃ ለብሰው ደካማውንና እየተሰደደ ያለውን ነፍስ ለመርዳት ሲመጡ ሰይጣንና ሰራዊቱ በጦርነቱ መሸነፋቸውን በመገንዘብ ወደ ኋላ ያፈገፍጋሉ፡፡ Review and Herald May 13, 1862.MYPAmh 41.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents