Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

መልዕክት ለወጣቶች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የመስቀል ኃይል

    ኢየሱስ ክርስቶስ በሰብዓዊ እጅ የሰብዓዊ ዘርን ለማቀፍ ሰብዓዊነትን የወሰደ ሲሆን በመለኮታዊው እጁ ደግሞ ዘላለማዊ የሆነውን አምላክ ዙፋን ጨበጠ። መስቀሉን በምድርና በሰማይ አማካይ ቦታ ላይ በመትከል እንዲህ አለ:- “እኔ ከምድር ከፍ ከፍ ባልሁ ጊዜ ሰዎችን ሁሉ ወደ እኔ እስባቸዋለሁ።” መስቀል የስበት ማዕከል እንዲሆን ነበር የታቀደው።MYPAmh 92.3

    መስቀሉ ያስፈለገው ለሁሉም ሰዎች ለመናገርና ውስን ሰውን ውስን ካልሆነው አምላክ ጋር ለማገናኘት ኃጢአት ከሰራው ገደል አልፎ ወደ ራሱ ለመሳብ ነበር። ሰው ከኃጢአት ጋር ከፈጠረው ጠንካራ ስምምነት ሊያላቅቀው የሚችለው የመስቀሉ ኃይል ብቻ ነው:: ክርስቶስ ራሱን የሰጠው ኃጢአተኛውን ለማዳን ነው። ኃጢአታቸው ይቅር የተባለላቸውና ኢየሱስን የሚወዱ ከእርሱ ጋር አንድነት ይፈጥራሉ። የክርስቶስን ቀንበር ይሸከማሉ። ይህ ቀንበር እንዲገታቸውና መንፈሳዊ ሕይወታቸውን እርካታ የሌለው የልፋት ሕይወት ለማድረግ አይደለም፤ በፍፁም አይደለም። የክርስቶስ ቀንበር የክርስቲያን ሕይወት የደስታና የፍስሐ መንገድ እንዲሆን የታቀደ ነበር፡፡ ክርስቲያን እግዚአብሔር አንድያ ልጁን አሳልፎ በመስጠት በእርሱ ያመነ ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲሆንለት እንጂ እንዳይጠፋ ማድረጉን በማሰላሰል መደሰት አለበት::MYPAmh 92.4

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents