Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

መልዕክት ለወጣቶች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የከበረ ንግግር

    በሳይንስ ትምህርቶች እጅግ የተማሩ ሰዎች ሁልጊዜ እግዚአብሔር የሚጠቀምባቸው ከሁሉ የተሻሉ መሣሪያዎች አይደሉም። መጽሐፍት ለየእለቱ ሕይወት ጠቃሚ የሆኑ እውቀቶችን የያዙ ሆነው ሳለ የእነዚህን መጽሐፍት እውቀት የማግኘት እድል የሌላቸውና ወደ ጎን የተተዉ ብዙ ሰዎች አሉ። እነዚያ ተማርን የሚሉ ሰዎች በራስ ብቃታቸው ስለሚተማመኑ ዓለም ከሚያውቃቸው መምህራን ሁሉ በላይ ከሆነው ከኢሱስ እንኳን ከመማር በላይ እንደሆኑ በማሰብ መማራቸውን ያቆማሉ።MYPAmh 270.1

    እነዚያ ያደጉና አእምሮአቸው የሰፋ፣ የማሰብ ችሎታቸው የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለማወቅ ካላቸው ፍላጎትና ቃሉን በጥልቀት ከመመርመራቸው የተነሣ የተሻሻለ ሰዎች ወደ ጠቃሚነት ደረጃ ይመጣሉ። የእግዚአብሔር ቃል በህይወታቸውና በባሕርያቸው መግቢያ አግኝቷል። በመሆኑም መገጣጠሚያዎችንና መቅኔን እስኪለይና የልብን ሀሰብና ፍላጎት እስኪመረምር ድረስ የተለየ ሥራውን መሥረት አለበት፡፡ ክርስቲያን ለእውነትና ለጽድቅ መጋደል እንዲችል በመንፈስና በአእምሮ ጠንክሮ እንዲያድግ የእግዚአብሔርን ቃል መመገብ አለበት።MYPAmh 270.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents