Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

መልዕክት ለወጣቶች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የሱስን ለማስደሰት መሻት

    ጌታ እያንዳንዳችን ልንፈፅምለት የሚገባን የተለየ ሥራ አለው:: የአለም እርኩሰት ወደ ፍትህ አደባባዮች ሲቀርብና በዕለታዊ ጋዜጣዎች ሲታተም ወደ እግዚአብሔር እንቅረብና የክርስቶስ ፀጋ በእኛ እንዲገለጽ በህያው እምነት ተስፋዎቹን እንጠማጠም:: በዓለም ውስጥ ተሰሚነት፣ ኃይለኛ ተሰሚነት ሊኖረን ይችላል:: የሰዎችን ጥፋተኝነት የሚያረጋግጥ የእግዚአብሔር ኃይል ከኛ ጋር እስከሆነ ድረስ በኃጢአት ውስጥ ያሉ ሰዎችን ወደ መለወጥ ልንመራ እንችላለን::MYPAmh 25.1

    የኛ ራስን ዝቅ ማድረግ በዚህ ስራ ብዙ አስተዋፅዖ ያደርጋል:: ትልቅ ሥልጣን ለመያዝና የሰዎችን ሙገሳ ለማግኘት መጣር የለብንም:: አላማችን ከሁሉም የበላይ ለመሆን መሆን የለበትም:: በእግዚአብሔር ክብር ላይ ያነጣጠረ ዓይን ሊኖረን ይገባል:: እግዚአብሔር በሰጠን እውቀት ሁሉ የእርሱ ፀጋ በኛ ላይ በመምጣት በመለኮታዊ አምሳያ እንዲቀርፀንና እንዲሰራን ራሳችንን በብርሃን መተላለፊያ ላይ በማስቀመጥ መሥራት አለብን:: በዚህ የምድር ታሪክ የመጨረሻ ቀናት የእግዚአብሔርን ሥራ ለመሥራት ራሳቸውን በሚቀድሱ ሰዎች ላይ የበለፀጉ በረከቶችን ለማፍሰስ ሰማይ በመጠባበቅ ላይ ይገኛል:: እንፈተናለን፣ ያለ እንቅልፍ ልናድር እንጠራ ይሆናል:: እነዚህ ጊዜያቶች እግዚአብሔር ማስተዋል እንዲሰጠንና የኛ የሆኑ መልካም ዕድሎችን ለይተን ማወቅ እንድንችል አእምሮአችንን እንዲያነቃቃው ልባዊ በሆነ ፀሎት ይለፉ::—The Review and Herald, April 1, 1909MYPAmh 25.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents